በሀገሬ ኢቨንት እና ፕሮሞሽን የተዘጋጀው በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ኢሬቻ ኤክስፖ በነገው ዕለት መስከረም 18/2017 በኤግዚቢሽን ማዕከል በድምቀት ይከፈታል።
በዙህ ኤክስፖ ባህላችን ይደምቅበታል፤ ከወዳጅ ዘመድ ጋር እንዝናናበታለን፤ ከባዛዙ ገብተን እንሸምትበታለን። በርካታ ድርጅቶችም ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው በኤክስፖው ይሳተፋሉ።
ሁሉም ዝግጅቶቻችን የኢሬቻን የፍቅርና የምሥጋና እሴት ለማሳየት የተለፋባቸው ናቸው። በተጨማሪም የዚህን ተወዳጅ ባህል ጠቀሜታ እና የወደፊት ሁኔታን የሚዳስስ የፓናል ውይይትም ይኖረናል።
በጉጉት የሚጠበቀው ልብን የሚያሞቀው #የሙዚቃ ኮንሰርታችንም ታዋቂ ድምጻዊያንን እንዲሁም ልዩ ዝግጅቶችን አካቶ ተሰናድቷል።